በከተማችን የመጀመሪያ የሆኑ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሠሩ የሕዝብ ትራንስፖርት አውቶብሶች ዛሬ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ፡፡

(አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፣ መጋቢት 16፣ 2016) የመጀመሪያዎቹ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሠሩ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ዛሬ ከቦሌ_በእስጢፋኖስ_አራትኪሎ_ሽሮሜዳ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

አውቶብሶቹን ወደ አገልግሎት ያስገባው ቬሎሲቲ ኤክስፕረስ የሚባል የግል ድርጅት ነው።

አውቶብሶቹ ከፍተኛ የህዝብ ፍላጎት ባለበት የስምሪት መስመር እንዲሰሩ የተደረገ ሲሆን፤ አንድ ጊዜ ቻርጅ ከተደረጉ በኃላ እስከ 370 ኪ.ሜ መጓዝ የሚችሉ ናቸው።

አውቶብሶቹም ዘመናዊና ምቹ ሲሆኑ፤ አሁን የከተማ አውቶብስ እየሰራበት ባለው የታሪፍ ተመን አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናል።

ቢሮው የግል ባለሀብቱ ወደ ዘርፉ እንዲቀላቀሉ ባደረገው መነሻነት ከቅርብ ቀናት በፊት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ 20 ሚኒባሶች አገልግሎት መስጠታቸው ይታወሳል።

ለበለጠ መረጃ፡

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ

ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et

ቴሌግረም፡-https://t.me/transport-bureau

Leave a Reply