የቃሊቲ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የአሠራር እና የብቃት ማረጋገጫ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 05/2010 ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ።

( የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ሚያዝያ 11/2016ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የከተማ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪዎች፣ የጭነት ትራንስፖርት ባለንብረቶች ድርጅት የአደረጃጀት፣ የአሠራር እና የብቃት ማረጋገጫ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 05/2010 መመሪያ አፈፃፀም ዙሪያ ዛሬ ውይይት አደረገ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ዘውዴ ቢሮው አገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽ ለማድረግ ቀደም ሲል በቢሮ ብቻ ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት በትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤተቶች መሰጠት መጀመሩን ገልፀው፤ አገልግሎቱን ማግኘት የሚፈልጉ ተገልጋዮች አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ብለዋል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት እና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ኤፍሬም ነዲ የመመሪያውን አስፈላጊነትና በመመሪያው የተቀመጡ ዋናና ዝርዝር ጉዳዮች ለባለድርሻ አካላት አቅርበዋል።

በተጨማሪው በመመሪያው መሰረት የጭነት ትራንስፖርት የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት መገናኛ በሚገኘው የትራንስፖርት ቢሮ እንደሚሰጥና በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እድሳት እንደሚሰጥ አቶ ኤፍሬም ገልፀዋል።

ተወያዮችም በቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች ውጤታማ እንዲሆኑ በቅንጅት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureauhttps://

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ዌብሳይት:-www.aactb.gov.et

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply