አገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፣ ሚያዚያ 08፣ 2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀሙን፣ የ100 ቀናት እቅዱንና የሪፎርሙን አተገባበር በተመለከተ ከአጠቃላይ የማእከል ሰራተኞች ጋር በጋራ ገመገመ፡፡

በእለቱም የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ በ100 ቀናት ሊሰሩ የየያዙ እቅዶችና የሪፎርሙ የዝግጅት፣ የተግባርና የቀጣይ አቅጣጫ የቀረበ ሲሆን፤ በቀረበው ሪፖርትና የ100 ቀናት እቅድ ዙሪያ የጋራ ውይይት ተደርጓል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ የከተማው አስተዳደር የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እና የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ እየሰራ ያለው ስራ ውጤታማ ለማድረግ በጊዜ የለኝም ስሜት መስራት እንደሚገባ በአንክሮ ገልፀዋል።

በሪፖርቱም በእቅድ ተይዘው የተከናወኑ ተግባራትን ከእቅዳቸው አንጻር አፈጻጸማቸው የተገመገመ ሲሆን፤ በዋናነትም በሪፖርቱ የብዙሀን ትራንስፖርት አቅርቦትን የማሳደግ ስራ፣ በአማካይ በየቀኑ 12,397 ተሽከርካሪዎች ማሰማራት መቻሉን፣ ባለው የትራንስፖርት አቅርቦት በቀን 3.34 ሚሊየን ጉዞ መፈጠር መቻሉን፣ 67,026 አጥፊ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን፣ የሞተር አልባ ትራንስፖርት የመሰረተ ልማት የማስፋት ስራ መሰራቱና በነፃ የስልክ መስመር የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት መቻሉን በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በውይይቱም በዘርፉ አገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ ለማድረግና የሰራተኛውን የመፈፀም አቅም ለመገንባት ሪፎርሙን ከመተግበር አንፃር የሪፎርም አደረጃጀቶችን መልሶ በማደራጀት በአገልግሎት አሰጣጥ ማንዋል መሰረት ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት ተገልጿል።

የቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureauhttps://

ዌብሳይት:-https://aatb.gov.et/en/home_en/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply