ከዊንጌት አደባባይ በእንቁላል ፋብሪካ እስከ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ያለው መንገድ ለብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት የተለየ መስመር (dedicated bus lane) መንገድ ስራ እንደሚጀምር ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከአጋር ተቋማት ከወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲቲዩት (World Resource Institute) እና ቫይታል ስትራቴጂስ (Vital Strategies) እንዲሁም ከአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ጋር በጋራ በመሆን ከዊንጌት አደባባይ በእንቁላል ፋብሪካ እስከ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ያለው መንገድ ለብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት የተለየ መስመር (dedicated bus lane) መንገድ ስራ አገልግሎት ነገ የሚጀምር ይሆናል።

በመሆኑም አሽከርካሪዎች ቀለም ተቀብቶ ለአውቶብስ ብቻ የሚል ፅሁፍ ያለበት መንገድ ላይ ከጠዋት ከ1፡00 ሰዓት እስከ ረፋድ 4፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ10፡00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ድረስ ለብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጋችሁ እንድታሽከረክሩ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳስቧል ።

የብዙሃን ትራንስፖርት አውቶብሶች፣ ሃይገር፣ ቅጥቅጥ እና የሚድ ባስ አሽከርካሪዎችም በተጠቀሰው ሰዓት በተፈቀደላችሁ መንገድ ብቻ በመጠቀም መንገዱ የታሰበለትን ዓለማ እንዲያሳካ እና አገልግሎት እንዲሰጥ የበኩላችሁን ኃላፊነት በአግባቡ እንድትወጡ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል::

ምንጭ:-ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

Leave a Reply