የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ 100 ዘመናዊ የከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አውቶብሶችን ስራ አስጀመረ።

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2015 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል የሚያስችሉ 100 ዘመናዊ የህዝብ ትራንስፖርት አውቶብሶችን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የከተማውን የህዝብ ትራንስፖርት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ ከተማ አስተዳደሩ ያቀረባቸው ዘመናዊ አውቶብሶች በከተማው የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ በመቀነስ ረገድ የማይተካ ሚና አላቸው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር እና ትራንስፖርት ለማግኘት የሚስተዋሉ ረጃጅም ሰልፎችን ለመቅረፍ በእቅድ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ቢሮ ኃላፊው አክለውም ዛሬ ወደ አገልግሎት የሚገቡት አውቶብሶች የጀመርነውን የብዙሀን ትራንስፖርት አቅርቦት እና ሽፋን ከፍ በማድረግ ወደ ብዙሀን ትራንስፖርት የምናደርገውን ሽግግር ከማፍጠኑ በዘለለ የትራንስፖርት ችግሩን ለመቅረፍ አይነተኛ ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል።

በተጨማሪም በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት አቅርቦት ችግር የበለጠ ለማቃለል ቀሪ 100 አውቶብሶች

በቅርብ ቀናት ገብተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

አውቶብሶቹ 3.8 ቢሊየን ብር ወጪ የተገዙ ሲሆን፤ ዘመናዊ ቴክኖሎጅ የተገጠመላቸው፣ የደህንነት ካሜራ፣ ለተሳፋሪው በጉዞ ወቅት የሚያገለግል (USB PORT)ሞባይል ቻርጅ ማድረጊያ ያለው፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለነፍሰጡሮች ምቹ የሆኑ ናቸው።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የካቢኔ አባላት፣ የከተማው ምክርቤት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር፣ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ከተማ የስራ ኃላፊዎች፣ የብራይተን ትሬዲንግ የመኪና አስመጪ ድርጅት አመራሮች፣ የቢሮው እና የተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች እና ጥሪ

የተደረገላቹ እንግዶች ተገኝተዋል።

ዘገባው:-የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ነው

Leave a Reply