37 ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅግ ዉጤታማ ፣ ደማቅ እና ውብ በሆነ ሁኔታ በሰላም ተጠናቅቋል::

ከተማችን ውብ ሆና እንግዶቿን እንድትቀበል መንገዶችን በማስዋብ አስተዋፅዖ ያበረከታችሁ ፤ ጉባኤው ከተጀመረበት እለት ጀምሮ አገልግሎት በመስጠት በፍጹም ኢትዮጽያዊ ጨዋነት እንግዶችን ስታስተናግዱ ለነበራችሁ ፤ የህብረቱ ጉባኤ ፍፁም ሰላማዊ በሆኑ መልኩ እንዲጠናቀቅ በተጠንቀቅ ሀላፊነታችሁን ለተወጣችሁ የፁጥታ አካላት ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Leave a Reply