የቦሌ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የስምሪት ማሻሻያ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አሳወቀ፡፡

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ፤ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የቦሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በክፍለ ከተማው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የኮድ አንድ ታክሲዎች በቁጥር ምን ያህል እንደሆኑ ለመለየት የኮድ አንድ ሚኒባስ ታክሲዎችን ቆጠራ እያደረገ መሆኑን አሳወቀ፡፡

የቦሌ ትንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የትራንስፖርት አገልግሎት ዳይሬክተር ኦቶ ሳላዲን የሱፍ ታክሲዎቹን በቁጥር ማወቅ ያስፈለነበት ዓላማ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ተሸከርካሪዎች በመለየት ትክክለኛ መረጃው ለመውሰድና አቅርቦትና ፍላጎትን ያማከለ የስምሪት ማሻሻያ ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡

በዛሬው እለትም የንስር የታክሲ ማህበር በአገልግሎት ላይ ያሉትን የሚኒባስ ታክሲዎች ብዛት ቆጠራ እየተደረገባቸው ሲሆን፤ በቆጠራውም ወቅት አገልግሎት ሰጪው በተሽከርካሪው ቀኝ በኩል የማህበሩ አባል ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የ2016 ዓ.ም ሰቲከር መለጠፉን፣ 3ኛ ወገን መኖሩን ህጋዊ ታፔላ መኖሩን፣ የታደሰ ቦሎ መለጠፉም እየተረጋገጠ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀውልናል፡፡

በቀጣይ ቀንም በብሌን የታክሲ ማህበር ስር የሚገኙ የኮድ 1 ታክሲ ብዛት ቆጠራ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረገጽ፡-https://www.aatb.gov.et

ፌስ ቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

Leave a Reply