በአዲሱ የሪፎርም አደረጃጀት ቢሮ ላይ ለተመደቡ አዲስ የስምሪትና የቁጥጥር ሰራተኞች ተቋማዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

(አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ሚያዝያ 1/2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ በአዲሱ ሪፎርም በምደባ ከሌላ ተቋም ለመጡ 76 የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪት ተቆጣጣሪ ሠራተኞች ወደ ስራ የሚያስገባ የአራት ቀናት ስልጠና ዛሬ መስጠት ጀምሯል፡፡

በእለቱ ስልጠናውን ያስጀመሩት የቢሮው የትራንስፖርት ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ዳዊት ዘለቀ በከተማ ደረጃ የተጀመረው ሪፎርም ውጤታማ እንዲሆንና የተሰማራችሁበት ሙያ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ በጥሩ ሙያዊ ስነምግባር ማገልገል እንደሚገባ በአንክሮ ገልፀዋል፡፡

ከስልጠናው በኃላም ሰልጠኞች የቢሮውን አጠቃላይ መዋቅራዊ አደረጃጀት፤ በዋናነትም የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪት ቁጥጥር ባለሙያዎች ተግባርና ኃላፊነት የሚያውቁና ከብልሹ አሰራር የፀዱ አገልግሎት ሰጪዎች እንዲሆኑ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የቢሮው አቅም ግንባታ ዳይሬክተር አቶ ኃይለማርያም ኃ/ሚካኤል ስልጠናው በአራት ርዕሰ ጉዳዮች ቢሮው በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፊነት፣ በፀገ ሙስናና ስነምግባር፣ በመንግስት የሰራተኞች አዋጅ 56/2010 እና የስምሪትና ቁጥጥር የስራ መዘርዝርና ተግባርና ኃላፊነት ዙሪያ ስልጠናው እንደሚሰጥ ገልፀው በእለቱን የስልጠና ዙሪያ ለሰልጣኞች ስልጠናውን ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናው በመስክ ምልከታዊ ስልጠና ጭምር እንደሚታገዝ ተገልጿል፡፡

ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureauhttps://

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply