በትራንስፖርት ቢሮ 9417 በነፃ የስልክ ጥሪ እየቀረቡ ያሉ የህዝብ ቅሬታዎች ምላሽ እየተሰጠባቸው መሆኑ ተገለፀ፡፡

(አዲስ አበባ ትራንፖርት ቢሮ፤ መጋቢት 09/ 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖት ቢሮ

ህብረተሰቡ በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በቢሮው ነፃ የስልክ ጥሪ መስመር 9417 ጥቆማዋችን በመቀበል ለህዝብ ቅሬታዎች ምላሽ እየሰጠ ይገኛል፡፡

በቢሮው የነፃ የስልክ ጥሪ ማዕከል ባለሙያዎች በቀን በአማካኝ 10 ቢሮውን የሚመለከቱ ጥያቄና አስተያየቶች እንደሚፈቱ ገልፀዋል፡፡

በነጻ የስልክ መስመሩ በድግግሞሽ የሚቀርቡ ቅሬታዎቹም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች መስመር ማቆራረጥ፣ ከታሪፍ በላይ ማስከፈል፣ መሳደብ እና ከተፈቀደው የመጫን አቅም በላይ በመጫን ተሳፋሪ ማጉላላት ሲሆኑ ሌሎችም ከተጠሪ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥና መረጃ ለመጠየቅ ወደ ጥሪ ማዕከሉ እንደሚደወል አስታውቀዋል፡፡

እነዚህን ጥቆማዎች መነሻ በማድረግም፤ ጥቆማው ወደ ተሰጠበት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት መረጃውን በመላክ ቅሬታው የሚፈታ ሲሆን፤ ህብረተሰቡም ከህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ጋር ተያይዞ ለሚኖረው አስተያየትና ጥቆማ ወደ ማዕከሉ ስልክ ሲደውሉ ጥፋት ያጠፋውን ተሽከርካሪ ሰሌዳ፣ የጉዞውን መነሻና መድረሻ እንዲሁም ሰዓቱን ጭምር መረጃ በመያዝ እንዲያቀርብ ተጠቁሟል፡፡

ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureauhttps://

ዌብ ሳይት:-www.aactb.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply