37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ እና ነገ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

———-

ጉባኤው “ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“ በሚል የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው የ2024 መሪ ሀሳብ ላይ ትኩረት አድርጎ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ሰላምና ደህንነት፣ ንግድና ትስስር፣ ተቋማዊ ማሻሻያዎች፣ ግብርና እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ ሰብዓዊ መብቶች፣ ስርዓተ ጾታና ወጣቶችን ማብቃት እንዲሁም የተቋማትና አደረጃጀቶች በጉባኤው ትኩረት ከሚሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል እንደሚሆኑ ተነግሯል።

በጉባኤው ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና የተቋማት ኃላፊዎች አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

Leave a Reply