የሞተር አልባ ትራንስፖርት ምንነት

የሞተር አልባ ትራንስፖርት አንዱ የትራንስፖርት አማራጭ ሲሆን የሚያካትታቸውም

🛑የብስክሌት

🛑የባለ ሶስት ጎማ ሞተር አልባ ብስክሌት

🛑የአካል ጉዳተኛ ዊልቸሮችን እና

🛑 የእግረኛ መንገድ ጭምር የሚያካትት ትራንስፖርት ነው።

የብስክሌት ትራንስፖርት ዘላቂ የሆነ የሞተር አልባ ትራንስፖርት አይነት ነው።

ብስክሌቶች በዝቅተኛ ዋጋ ከአየር ብክለት ነፃ የሆነ አገልግሎት እና መኪና ሊይዘው ከሚችለው ስፍራ አንደ አስረኛውን የሚይዙ መጓጓዣዎች ናቸው።

በዋናነትም ኢትዮጵያን ከውጭ ከሚመጣ ነዳጅ ጥገኝነት ለመቀነስ እና በሞተር ተሽከርካሪ ከሚመጣ የካርበን ልቀት በ2030 ነፃ እንድትሆን ታልሞ እየተሰራ ይገኛል።

ከዚህም በተጨማሪ ብስክሌት ብቻ በተለየ መንገድ ብስክሌት መጠቀም የግል ሞተር ተሽከርካሪን ከመጠቀም የተሻለ ሲሆን በተለየ መልኩ ከአጭር እስከ መካከለኛ ርቀት ላላቸው ጉዞዎች አመቺ ነው።

Leave a Reply