የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት የኃይል ማስተላለፊያና የመገናኛ ኬብሎችን የሰረቀ ግለሰብ በ6 አመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት መቀጣቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ግለሰቡ በፈፀመው ወንጀል ድርጅቱ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት እንደደረሰበት ተገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ የጋራ መገልገያ በሆኑ የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች አስቀድሞ ለመከላከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኬብሎች ላይ…