በኮሪደር ልማቱ የተነሱ የልማት ተነሺዎች እንዴት ተስተናገዱ?

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሰሞኑ የኮሪደር ልማቱን አስመልክተው ከሰጡት መግለጫ የተወሰደ፦

👉ከምትክ ቦታ ጋር በተያያዘ ሰፊ ቦታ ያስፈልገናል ያሉትን በኮልፌ ቀራንዮ፣ ጉለሌ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ቦታዎች ተሰጥቷቸዋል፡፡

👉በከተማዋ መሀል አካባቢዎች መቆየት ነው የምንፈልገው ያሉትን ቂርቆስ፣ልደታና አዲስ ከተማን የመሳሰሉ መሀል ከተሞች ላይ ባሉ ኪስ ቦታዎች እንዲስተናገዱ ተደርጓል ፡፡

👉ከቀበሌና ከኪራይ ቤት ውጪ ያሉ ቤቶች ከመኖሪያ ቤት ግንባታቸውን እስከሚፈጽሙ የአንድ አመት የቤት ኪራይና የማጓጓዣ ክፍያ ተፈፅሟል ፡፡

👉የቀበሌ ቤቶችንና የኪራይ ቤቶችን ተከራይተው ሲሰሩ የነበሩ ሰዎችም ተደራጅተው የንግድ ስራቸውን ሊያስቀጥልላቸው በሚችል አካባቢ ቋሚ መስሪያ ቦታ እንዲያገኙና ባለይዞታ እንዲሆኑ ተደርጓል ፡፡

👉ከመንገድ ወደ ውስጥ ሆነው የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ የነበሩ ወደ 551 ለሚሆኑ ሰዎችም አሁን ከሚሰሩበት የተሻለና ሰፋ ያለ የመስሪያ ሼድ እንዲሰጣቸው ተደርጓል ፡፡

👉አራዳ ክፍለ ከተማ አካባቢ ብቻ 1ሺህ 400 የሚደርሱ ዜጎች የጋራ መኖሪያ ቤት መርጠው ቋሚ የቤት ባለቤት በመሆን የተሻለ ህይወት መምራት ችለዋል ፡፡

👉መክፈል አንችልም በኪራይ ቤት ነው የምንቀጥለው ያሉ 402 ነዋሪዎችም አቃቂ አካባቢ ከተገነቡ ተገጣጣሚ ቤቶች ውስጥ እጅግ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ማድረግ ተችሏል፡

Leave a Reply