ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል እንደሚቻል ተገለፀ።

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ መጋቢት 19/2016ዓ.ም ) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን በ9ወራት በቅንጅት በጋራ የተሰሩ ስራዎችንና የመጡ ተጨባጭ ለውጦችን በጋራ ገምግሟል።

በውይይቱም ከተማዋ ለተያያዘችው ሁለንተናዊ ዕድገት

ተቋማት የእርስ በእርስ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

በውይይቱም ከስራ ፈጠራ እና ክህሎት፣ ከዘመናዊ የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ ከፀጥታ እና ደህነንት፣ ከመሠረተ ልማት ዝርጋታ ጋር ተያይዞ የሚሠሩ ስራዎችን እንዲሁም ከህገወጥ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ በቅንጅት በመሰራቱ ውጤት ማምጣት መቻሉ ተጠቁሟል።

በመጨረሻም የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል በቀጣይ በጋራ የሚሰሩ ስራዎችን አቅጣጫ ተቀምጧል።

በውይይቱም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የስራ ኃላፊዎች፣ከሰላምና ፀጥታ ቢሮ፣ ከፖሊስ ኮሚሽን፣ ከፍትህ ቢሮ፣ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ፣ ፋይናንስ ቢሮ፣ ንግድ ቢሮ እና ስራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ሆነዋል።

ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureauhttps://

ዌብ ሳይት:-www.aactb.gov.et

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply