ሰራተኞች በኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ ያለውን ግንዛቤ በማዳበር በቫይረሱ ሰላባና ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመታደግ የበኩላችንን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ተጠቆመ፡፡ (የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የካቲት 07 ቀን 2016ዓ.ም)

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ በተመለከተ በማዕከል እና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለሚገኙ ሰራተኞች ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ለሁለት ቀናት ስልጠና በተደረገበት ወቅት እንደተገለፀው ሰራተኛው ራሱን ከበሽታው በመከላከል በቫይረሱ ሰላባና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መታደግ እንደሚገባ ተገልል፡፡

ስልጠናው በኤች አይ ቪ/ኤድስ የሞቱ አካላትና ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ህፃናትና ቤተሰቦቻቸውን ለማስታወስ አንዲሁም ህብረተሰቡ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ምርመራ በማድረግ እራሱንና ወገኑን ከ በሽታው መታደግ እንደላበት ለማሳሰብ ታቅዶ የተዘጋጀ ነው፡፡

ስለሆነም ሰራተኞች የበኩላቸውን ሚና በመወጣት በተለይ በቫይረሱ ስላባና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መታደግ እንዳለበቸውም በስልጠናው ወቅት ተጠቁሟል፡፡

Leave a Reply