ሪፎርም ካደረጉ 16ቱ ተቋማት ጋሩ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሪፎርም በተደረጉ ተቋማት የተጀመረውን የትግበራ ምዕራፍ ውጤታማ በማድረግና በትኩረት በዝግጅት ምዕራፍ የተጀመሩ ስራዎችን በማስቀጠል እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራን ለማከናወን ብሎም የተጀመረውን ስራ ለማስተግበር የሚረዳ የመግባቢያ ሰነድ በዋናነት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ፣ ሪፎርም ከተደረጉ 16ቱ ተቋማት አስተግባሪ ግብረ ሀይል እና ከክ/ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊዎች ጋር ተፈራርሟ፡፡

የስምምነት ሰነዱ በዋናነት የተግባር ምዕራፍ ስራዎችን ትኩረት በመስጠት እና ተጠያቂነትን በማስፈን እንዲሁም አገልግሎቶችን ዘመናዊና ቀልጣፋ በማድረግ የተቋማትን አገልግሎት በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ተፈላጊውን አገልግሎት በተፈላጊው ፍጥነት ለመስጠት መሆኑ ተገልጿል።

ዘገባው የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ነዉ

Leave a Reply