ለብልሹ አሰራር ተጋላጭ ለሆኑ የስራ ክፍሎች በሙያዊ ስነ ምግባር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2015/ዓ.ም፤ በትራንስፖርት ቢሮ ለብልሹ አሰራር ተጋላጭ ለሆኑ የስራ ክፍሎች የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ በመላበስ አገልግሎት ስለመስጠትና በህይወት ክህሎት ግንዛቤ ዙሪያ የግምሽ ቀን ስልጠና ተሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የስነምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አምባላይ ዘርዓይ ቢሮው በዘርፉ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልፀው፤ ባለሙያው አገልግጋይነት ትልቅ ኃላፊነት መሆኑን በመገንዘብ ህዝብና መንግስት የጣለበትን ይህንን ኃላፊነት ፍፁም ሙያዊ ስነምግባር በመላበስ ችግር ፈቺ እንዲሆን የዛሬው ስልጠና ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

ቢሮውም በበጀት አመቱ የሰራተኛውን አቅም ለመገንባት በርካታ የስራ ላይ ስልጠናዎችን እያዘጋጀ ሲሆን፤ በቀጣይም በዚህ ለብልሹ አሰራር ተጋላጭ የሆኖ ስራ ክፍሎች ቀጣይነት ያለው ተከታታይ ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

Leave a Reply