የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የህጻናት ማቆያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

መጋቢት4/2015፤ አዲስ አበባ፤ በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 36(1)(ሐ) መሰረት ህፃናት ከወላጆቻቸው ማግኘት የሚገባቸውን እንክብካቤ በተለይም የእናት ጡት ወተት የማግኘት መብታቸውን ለማረጋገጥ ወላጅ ሴት የመንግስት ሰራተኞች ልጆቻቸውን በሚሰሩበት አካባቢ የሚያቆዩበትና ጡት የሚያጠቡበት ሁኔታ ማመቻቸት አስፈላጊ ሆኖ ተገልፆል፡፡

በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሴት ሰራተኞች በመውለዳቸው ምክንያት ከስራ ገበታቸው እንዳይቀሩና በስራቸው ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ በተቋሙ ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ በአንድ ጊዜ ከአስራ አምስት እስከ 20 ህጻናቶችን መያዝ የሚችል ንፁህና ምቹ 2 የመኝታ ቦታዎች፣ የመመገብያና የማጥባያ ክፍል ፣የነርስ ክፍልና የመጫወቻ ክፍልና በርካታ የልጆች መዝናኛና ትምህርት ሰጪ መጫወችና ሁለት የመፀዳጃ ቤቶችን በማዘጋጀት ማእከሉ እንዲመረቅና አገልግሎት እንዲጀመር ተደርጓል፡፡

የተቋሙ ሴት ሰራተኞችም የህጻናት ማቆያው መከፈቱ ያለምንም ስጋትና ሃሳብ ሙሉ ኃይላቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ጊዜያቸውን ተጠቅመው ውጤት እንዲያስመዘግቡና ሴት የመንግስት ሰራተኞች ትውልድን የመተካት ሃላፊነታቸውን ሲወጡ ህጻን ልጃቸውን ለመንከባከብ በሚል ስራ እንዳያርጡ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡

በምርቃት ፕሮግራሙ የቢሮው ኃላፊ፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች፣ ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ተወካይ፣ የተቋሙ ሰራተኞችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Leave a Reply