የትራንስፖርት ሚኒስትሩና የቢሮ ኃላፊው የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን ተዘዋውረው ተመለከቱ

(አ.አ ግንቦት 7/ 2015 ዓ.ም) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር በስራ መውጫ ሰአት ላይ ያለውን የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ምልከታ አድርገዋል፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት በሚጠብቁ ተገልጋዮች በብዛት የሚገኙባቸውንና ረጃጅም ሰልፍ የሚስተዋልባቸውን ሜክሲኮ፣ ቦሌ እና መገናኛ አካባቢዎች ቅኝት ያደረጉ ሲሆን በርካታ ክምችት ባለባቸው ቦታዎች አስቸኳይ የትራንስፖርት ስምሪት እንዲሰጥ አድርገዋል፡፡

ቅኝት ባደረጉባቸው አካባቢዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት የሚጠብቁ ተገልጋዮችን በከተማዋ ስላለው የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ አነጋግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻልና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሰረተና ቀጣይነት ያለው ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ምንጭ:-የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

Leave a Reply