“ዛሬ ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ካሉ አመራሮች ጋር የስራ ግምገማ በአድዋ ድል መታሰቢያ ፓን አፍሪካን አዳራሽ ማካሄድ ጀምረናል።

ባለፉት ሰባት ወራት በርካታ ያሳካናቸው እና ውጤታማ የሆኑ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም ከህዝብ ጥያቄ አንጻር አሁንም በርካታ ክፍተቶች እና ርብርቦችን የሚጠይቁ ስራዎች አሉብን።

በሰባት ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማችን መፈጸም ሲገባቸው ያልተፈጸሙ ስራዎች ፣ ጉድለቶቻችን እና መንስኤዎቻቸውን በመለየት የማስተካከያ አቅጣጫ በማስቀመጥ ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ እዲሁም መልካም አፈጻጸማችንን በማላቅ በቀሪ ወራት ተጨማሪ አቅም ፈጥረን ለተሻለ ዉጤት የምንዘጋጅበት መድረክ ይሆናል።”

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Leave a Reply