በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የቂርቆስ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አገልግሎት አሰጣጡን ጎበኙ

(አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ሰኔ 13/2016ዓ.ም) በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር፣ የከንቲባ አማካሪ አቶ ፋሲል ወልደ/ማርያም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የሪፎርም ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ በቀለ ተመስገን፣ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ደሳለኝ ተረፈ እንዲሁም የተቋሙ አመራሮች ከሪፎርም ትግበራ በኃላ የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አገልግሎት አሰጣጥን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር በሪፎርሙ መነሻነት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆኑንና የከተማ አስተዳደሩ አገልግሎቱን ለማሻሻል አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል ብለዋል።

የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግስት አሰፋ የአገልግሎት አሰጣጡን ከማዘመን እና ዲጂታላይዝ ከማድረግ አኳያ የተተገበሩ ዋና ዋና አገልግሎቶችን በዋናነትም ዘመናዊ የደንበኞች አስተያየት መስጫ፣ ቅሬታ ማቅረቢያና የደንበኞች ዕርካታ መለኪያ መሳሪያዎችን እና ዘመናዊ የወረፋ ማስጠበቂያ ሲስተምን አስጎብኝተዋል።

በተጨማሪም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ የደህንነት ካሜራዎችን በመግጠሙ ብልሹ አሰራሮችን እና ድርጊቶችን ለመቆጣጠር እንደሚያስችለው ተገልጿል።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎችም በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ስራ መሰራቱን በማበረታታት፤ ይህ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና ጽህፈት ቤቱ በከተማ ደረጃ ሞዴል በመሆን ለሌሎች መስሪያ ቤቶች ተሞክሮዎችን ማካፈል እንደሚገባው ጠቁመዋል።

ለተጨማሪ መረጃ

ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ለበለጠ መረጃ፡- 011-666-33-74 ወይም

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply