በመንገድ መሠረተ ልማትና በትራንስፖርት አቅርቦት በግማሽ ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት፡-

——–

👉 የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታ ስራዎች ጋር በተያያዘ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ስራዎች 19.17 ኪ.ሜ ለማከናወን ታቅዶ 16.39 ኪ.ሜ (85%)፣ 4.95 ኪ.ሜ የኮብል ስቶን የመንገድ ግንባታ በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ለማከናወን ታቅዶ 4.45 ኪ.ሜ (89.90%) ተከናውኗል፣

👉 15.9 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ ግንባታ ስራ ለማከናወን ታቅዶ 12.71 ኪ.ሜ (80.4%)፣ 2 ኪ.ሜ የፈጣን አውቶቡስ መንገድ ለመገንባት ታቅዶ 5.91 ኪ.ሜ (295.5%)፣ 15 ኪ.ሜ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ የእግረኛ መንገድ ለመገንባት ታቅዶ 27.6 ኪ.ሜ (184%) ተከናውኗል፣

👉ኘሮጀክቶቹ ከ2ዐ ኪሎ ሚትር በላይ እርዝመትና እስከ 43 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት ያላቸው ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የመንገድ ግንባታ ኘሮጀክቶች በመሆናቸው የከተማ መንገድ ስታንዳርዱን ከፍ ያደረጉና የትራፊክ መጨናነቅን የሚቀንሱ ናቸው፣

👉 በተለያዩ የከተማዋ ማዕዘናት እየተገነቡ በሚገኙ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከ2300 ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ግዙፍ ተሸጋጋሪ እና የወንዝ መሻገሪያ ድልድዮች እየተገነቡ ሲሆን የትራፊክ አደጋን የሚቀንሱ 27.6 ኪ.ሜ እርዝመት ያላቸው የእግረኛ እና የሞተር አልባ ትራንስፖርት አፈፃፀማቸውም ጥሩ በመሆኑ በዚህ ዓመት አብዛኞቹን ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፣

👉 የብዙሀን ትራንስፖርት(አውቶብስ) አቅርቦት በማሳደግ የአገልግሎት ጥራት በማሻሻል እየተሰራ ሲሆን 67 አዳዲስ አውቶብሶች ወደ ስምሪት በማስገባት በቀን በአማካይ 1033 አውቶብሶችን ወደ ስምሪት እንዲገቡ ማድረግ የተቻለ ሲሆን 944 አውቶብሶችን በጂፒኤስ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ቁጥጥር በማድረግ የአገልግሎት ውጤታማነትን ለማሻሻል ከፍተኛ ስራዎች ተሰርተዋል፤

Leave a Reply