የ BRT መስመር 4 እና የ BRT መስመር 3 የአዋጭነት ጥናት የማስጀመሪያ ስብሰባ (Kick Off Meeting) ተደረገ።

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ፤ሰኔ 11/2016) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የከተማዋን የትራንስፖርት ስርዓት የተሻለ ለማድረግ ከኮሪያ የልማት ድርጅት በተገኘ ድጋፍ የ BRT መስመር 4 እና የ BRT መስመር 3 የአዋጭነት ጥናት እንዲከናወን ለማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ እነዚህ የ BRT ልማቶች ከተማዋ ለምታስበው የስማርት ሲቲ ትግበራና የብዙሃን ትራንስፖርትን ችግር ከመፍታት አኳያ ወሳኝ በመሆናችው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት በመስጠት በትብብር መስራት ይገባዋል ብለዋል፡፡

የሁለቱ የፈጣን አውቶብስ መስመሮችም አጠቃላይ እርዝመት 36.5 ኪ.ሜ ገደማ የሚደርስ ሲሆን የ BRT መስመር 4 ከሽሮሜዳ ተነስቶ ለገጣፎ አደባባይ እንዲሁም የ BRT መስመር 3 ደግሞ ከአዲሱ ገበያ ተነስቶ ሃና ማሪያም የሚደርስ መስመር ሲሆን፤ በዛሬው እለት የአዋጭነት ጥናት እንዲያከናውን ከተመረጠው አለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ጋር የጥናት ስራ ማስጀመሪያ ስብሰባ (Kick Off Meeting) ተከናውኗል፡፡

በውይይቱም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፣ የኮሪያ ኢክስፖርት ኢምፖርት ባንክ (Korea EXIM Bank) የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን፣ የአዲስ አበባ ፕላንና ልማት ቢሮ፤ የአዲስ አበባ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ እንዲሁም ሌሎች የተቋማት ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።

Leave a Reply