9417 ነፃ የጥሪ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 06፤ 2014፤ በመዲናዋ በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥሙ ችግሮች የጥቆማ መስጫ ነፃ የጥሪ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት እና መሰል በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ተገልጋዩ ህብረተሰብ ጥቆማ፣ አስተያየትና ሃሳብ የሚሰጥበት 9417 ነፃ የስልክ መስመር ይፋ ሆኗል፡፡
ቢሮው በትራንስፖርት አገልግሎት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በተለይ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡
በመሆኑም የትራንስፖርት ተገልጋዩ ህብረተሰብ በማንኛውም እንቅስቃሴ ወቅት የሚያጋሙ ችግሮችን ለቢሮው መረጃ ለመስጠት ከዚህ ቀደም በመደበኛ የቢሮ ስልክ መስመር ይጠቀም የነበረ ሲሆን አሁን ይህን በመቅረፍ 9417 ነፃ የጥሪ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
ስለሆነም ማናቸውንም የትራንስፖርት ዘርፍ የሚመለከቱ ጉዳዮችን በነፃ የጥሪ መስመራችን 9417 እንድታሳውቁ ቢሮው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ዘገባው፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 011 666 33 74
የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/tpmo
ኢ-ሜይል፦ aagtpmo@gmail.com

Leave a Reply