የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት መረጃ የማሰራጨት ስራን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አሳሰቡ፡፡

የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት መረጃ የማሰራጨት ስራን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አሳሰቡ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012፤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ከፌደራልና ከክልል ኮሙዩኒኬሽን አመራሮች ጋር በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተወያይተዋል።

የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ማስረጃን መሰረት ያደረገ መረጃን በማሰራጨት ለመከላከል እና ስርጭቱን ለመግታት የማይተካ ሚና እንዳላቸው አስታውቀዋል።

በየደረጃው ለሚገኘው ሕዝብ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን በማስተላለፍ የማረጋጋት ሚናን ከመጫወት አንፃር የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ወሳኝ ድርሻ አላቸው ብለዋል።

በዕለቱም በኮሮና ቫይረስ (በኮቪድ -19) ግንዛቤ የማሳደግ ጥረቶች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን፥ የፌደራልና የክልል ኮሙዩኒኬሽን አመራሮች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

Leave a Reply