የአዲስ ከተማ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር አጠናክሮ ቀጥሏል።

(የትራንስፖርት ቢሮ፤ ግንቦት 22/2016ዓ.ም) የትራንስፖርት ቢሮ የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የኦፕሬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ግርማ ደበሌ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ያሉባቸውን ቦታዎች በመለየት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የመልካም አስተዳደር ችግር በፈጠሩ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የድንገተኛ የቁጥጥር ስራ መደረጉን ገልፀዋል።

ዛሬ በተደረገው የቁጥጥር ስራም የአዲስ ከተማ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ከትራፊክ ፖሊስ፣ ከትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን የተሰራ ሲሆን፤ ከተሰጠው የስምሪት መስመር ውጭ፣ ከታሪፍ በላይ ባስከፈሉ፣ ትርፍ ጭነው የተገኙ እና ተሳፋሪዎችን ሲያጉላሉ የነበሩ 55 ተሽከርካሪዎች እና የአገልግሎት ፍቃድ ያልተሰጣቸው 4 ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ የማስተማሪያ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

አገልግሎት ሰጪዎችም በአገልጋይነት መንፈስ ህዝብን የማገልገል ግዴታ እንዳለባቸውና ህብረተሰቡም ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር ተያይዞ ለሚኖረው አስተያየትና ጥቆም ለስምሪት ቁጥጥር ሰራተኞች፣ ለትራፊክ ፖሊስ፣በ ነፃ የስልክ መስመር 9417 የአጥፊ አሽከርካሪውን የሰሌዳ ቁጥር በመያዝ ወይም አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ቢሮ ቁጥር 505 በአካል በመቅረብ ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ያሳውቃል።

ለተጨማሪ መረጃ

ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ለበለጠ መረጃ፡- 011-666-33-74 ወይም

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply