20 አዳዲስ የኤሌክትሪክ ሚኒባሶች የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ የካቲት 11/2016ዓ.ም ) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትን ለማሻሻልና ተደራሽ ለማድረግ የግል ባለሀብቱ ወደ ትራንስፖርት ዘርፉ እንዲቀላቀል በፈጠረው እድል ዛሬ ሀያ /20/ አዳዲስ የኤሌክትሪክ ሚኒባስ ታክሲዎችን በነበረው የስምሪት መስመርና ታሪፍ ከቦሌ-በሚሊኒየም-በስቴድዮም-ሜክሲኮ (ቡናና ሻይ ) እና ከቦሌ-በሚሊኒየም-በጊዮን_ፒያሳ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን በዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖች መሰጠቱ የህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦቱን ከማሻሻሉ በተጨማሪ የበካይ ጋዝ ልቀት በመቀነስና ከተማዋን የሚመጥንና ውብ ገፅታ ከመገንባት አንፃር የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው።

ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureau

ድረገጽ፦ https://www.aatb.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply