የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቅቋል፡፡

ምክር ቤቱ በሁለተኛ ቀን ውሎው በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቀረቡ የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል፡፡

በዚህም ፤-

1. አቶ ያብባል አዲስ ጎበዜ -የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ

2. አንድነት ብዙሰው ታመነ- የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር

3. አቶ ቁሴ ለታ ዋቅጅራ- የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር

4. ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ

5.ወ/ሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

6. አቶ ማሾ ኦላና- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሆነው እንዲያገልግሉ ተሹመዋል፡፡

የስራ ኃላፊዎቹ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

Leave a Reply