የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ዋና ዋና ተግዳሮቶችና መፍትሔዎቻቸው ላይ በተደረገ ጥናት ላይ ውይይት ተደረገ።

ነሐሴ 13/2016 ዓ.ም (ትሎሚ):- የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ፣ ክቡራን ሚኒስትር ዲኤታዎች፣የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ዋና ዋና ተግዳሮቶችና መፍትሔዎቻቸዉን ላይ የተደረጉ ሁለት ጥናቶች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ የዉይይቱ ዓላማ የዘርፉን ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በተጠናው ጥናት ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ መሆኑን ተናግረዋል።

አክለውም ሴክተሩ ተልዕኮዉን በሚገባ እንዳይወጣ ማነቆ የሆኑ ተግዳሮቶችን በመለየት በዘላቂነት እንዲፈታ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በቀረቡ ጥናቶች ላይ ተጨማሪ ግብአት ሰጥተዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ አገልግሎት በሚፈለገው ደረጃ ውጤት እንዲያስመዘግብ እና ተወዳዳሪ እንዲሆን ዘርፉን ሪፎርም ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል።

@የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

Leave a Reply