የቢሮ አመራርና ሰራተኞች በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ መትከል ማስጀመሪያ መርሐ -ግብር 10,000 የዛፍ ችግኞችን ተከሉ።

የቢሮው አመራሮች እና ሠራተኞች በዛሬው ዕለት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በተለምዶ መንዲዳ በሚባል ስፍራ “የምትተክል ሃገር የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደዋል፡፡

መርሀ ግብሩን በይፋ ያስጀመሩት የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ በየአመቱ በከፍተኛ ንቅናቄ እየተካሄደ የሚገኘው የችግኝ ተከላ ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ መሆኑንና ችግኞቹ የሀገሪቱን ስነምህዳር ለመጠበቅ እና ለዘላቂ ሀገራዊ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደረግ ነው ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም የትራንስፖርት ዘርፉ ለካርበን ልቀት ሊያሳድር የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመከላከል የአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብሩ ወሳኝ ድርሻ አለው ስለሆነም የሚተከሉት ችግኞችን በአግባቡ በመትከል በመንከባከብ እና በመጠበቅ ሁሉም ድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

በዘንድሮ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሩ 30,000 ችግኝ በቢሮ ደረጃ የሚተከል ሲሆን፤ በቀጣይ መርሀ ግብር ቀሪ 20,000 ችግኞች የሚተከሉ ይሆናል።

Leave a Reply