በከተማችን ዘመኑ የሚጠይቀውን ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ ተቋሞቻችንን በቴክኖሎጂ እና የተለያዩ አቅርቦቶችን በማሟላት እንዲሁም በማብቃት ላይ እንገኛለን::
በአንድ በኩል መሰረተ ልማት እየዘረጋን በሌላ በኩል የአየር ብክለትን እና ሙቀትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸው ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ አገልግሎትን እያሳለጥን ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማ የመገንባት ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ




