የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ በተመለከተ በማዕከል እና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለሚገኙ ሰራተኞች ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ለሁለት ቀናት ስልጠና በተደረገበት ወቅት እንደተገለፀው ሰራተኛው ራሱን ከበሽታው በመከላከል በቫይረሱ ሰላባና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መታደግ እንደሚገባ ተገልል፡፡
ስልጠናው በኤች አይ ቪ/ኤድስ የሞቱ አካላትና ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ህፃናትና ቤተሰቦቻቸውን ለማስታወስ አንዲሁም ህብረተሰቡ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ምርመራ በማድረግ እራሱንና ወገኑን ከ በሽታው መታደግ እንደላበት ለማሳሰብ ታቅዶ የተዘጋጀ ነው፡፡
ስለሆነም ሰራተኞች የበኩላቸውን ሚና በመወጣት በተለይ በቫይረሱ ስላባና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መታደግ እንዳለበቸውም በስልጠናው ወቅት ተጠቁሟል፡፡


