ጥቅምት 24 ፣ 2013 የሰሜን ዕዝ የተጠቃበት 2ኛ ዓመት መታሰቢያ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚዘከር የመከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ

በአሸባሪው ህወሓት ክህደት ጥቅምት 24፣ 2013 የሰሜን ዕዝ የተጠቃበት 2ኛ ዓመት መታሰቢያ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚዘከር የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የጥቅምት 24 ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ በተመለከተ የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ዕለቱ በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ደረጃ ጨምሮ ሰራዊቱ ባለበት የተለያዩ አካባቢዎች በልዩ ሁኔታ ታስቦ እንደሚውል ኮሎኔል ጌትነት በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡

ጥቅምት 24ን ስናስብ ቂም እና ጥላቻን ለማብቀል ሳይሆን መጪው ትውልድ ይህንን የሀገር ክህደት እንዲረዳው እና እንዲማርበት መሆኑንም ኮሎኔል ጌትነት በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡

Leave a Reply