የኮድ 3 የተሽከርካሪ ስምሪት የሽክርክሪት መርሀ-ግብር ውጤታማ በሆነ መልኩ እያከናወነ መሆኑን የትራንስፖርት ቢሮ የለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ግንቦት 13/2016ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የለሚ ኩራ ቅርንጫፉ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኢንሰፔክተር ቶማስ ሄርጶ አገልግሎት ሰጪው አገልግሎቱን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲሰጥ በየሶስት ወሩ የሚካሄደውን የተሽከርካሪዎችን ስምሪት ድልድል ቀልጣፋና እና ግልፅ የሆነ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት የቅድመ ዝግጅት ስራ ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጋር የሰራ ሲሆን፤ ተገልጋዩ አገልግሎቱን ያለወረፋ እንዲያገኝ የተሽከርካሪ የመጨረሻ ሰሌዳ ቁጥራቸውን መነሻ በማድረግ በሙሉ እና ጎዶሎ ቁጥር አገልግሎት የሚያገኙበትን የጊዜ ሰሌዳ በመለያየት አገልግሎቱን እየሰጠ ነው፡፡

አሰራሩም ተገልጋዮች በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ በመምጣት ለአላስፈላጊ እንግልት እንዳይዳረጉ ከማድረጉም ባሻገር የአገልግሎት አሰጣጡ እንዲቀላጠፍ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ የንብረት አመዘጋገብ ሂደቱንም በተለየ መልኩ አዲስ አሰራር ከተጠያቂነት ጋር በመዘርጋት ውጤታማ ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡

አገልግሎቱን ሲጠቀሙ የነበሩ አሽከርካሪዎችም የተዘረጋው አዲስ አሰራር በተቀመጠላቸው ጊዜ መሰረት በመምጣት የተቀላጠፈ እና ግልፅ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኙ ማደረጉንና ይህም ከዚህ በፊት በነበሩት የሽክርክሪት ፕሮግራሞች ይታይ የነበረውን እንግልት እንደቀረፈላቸው ተናግረዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et

ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureauhttps://

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply