የኮድ ሶስት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች የሽክርክሪት ሶፍትዌር አገልግሎት ስራ ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፤ 2014፤ የኮድ ሶስት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ረዘም ላለ ጊዜ ሲያነሱት የነበረ የአስራ አራተኛው /14ኛው/ የስምሪትና ሽክርክሪት ሶፍትዌር አገልግሎት ስራ የቅድመ ዝግጅት ስራው በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ወደ ስራ እንደሚገባ የቢሮው የተቋማት አቅም ማጎልበትና ስልጠና ቡድን መሪ አቶ አብርሀም አድነው ገልፀዋል፡፡

ሶፍትዌሩ የኮድ ሶስት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በየሶስት ወሩ በሽክርክሪት ወይም በዙር አገልግሎቱን በፍትሀዊነት እንዲሰጡ የሚያስችል ነው።

አገልግሎቱ በሽክርክሪቱ ሶፍትዌር መሆኑ በርካታ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን፤ የስምሪትና ድልድል ባለሙያው መጀመሪያ ባስገቡት ዳታ /መረጃ/ መሠረት ያለ አድሎ ተሽከርካሪዎች በተለያዩ መስመሮች ተሰማርተው ከሰው ንክኪ ፀድቶ ለህብረተሰቡ ፍትሀዊ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ያስችላል፡፡

በመጨረሻም ወደ ትግበራ ለመግባት እንዲረዳ የቢሮው የተቋማት የጥናትና አቅም ማጎልበትና ስልጠና ቡድን መሪ ከተቀናጀ ሲስተም ጥናት ዳይሬክቶሬት በጋራ በመሆን ለአምስት ቀናት ለአስራ አንዱም የቢሮው ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ለተውጣጡ በድምሩ ሀያ ሁለት ስምሪትና ድልድል ባለሙያዎች በሶፍትዌሩ አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቶል።

ዘገባው፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

ነፃ ስልክ ፡-9417 ይደውሉ

የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

Leave a Reply