የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ትርፍ የሚጭኑ ባለታክሲዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ትርፍ የሚጭኑ ባለታክሲዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው

መጋቢት 10፣ 2012፤ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ትርፍ የሚጭኑ ባለታክሲዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡

ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ የሕዝብ አገልግሎት ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እና ባለታክሲዎች መጨናነቅ እንዳይፈጥሩ መመሪያ ተላልፎላቸው መመሪያውን ጠብቀው ሥራቸውን እንዲያከናውኑ የተነገረ ሲሆን፣ አሠራሩን የአውቶቡስ አገልግሎት ሰጪዎች ተግባራዊ ቢያደርጉትም ታክሲዎች እና ሚኒባሶች ሕጉን እያከበሩ አለመሆኑ ተገልጿል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ በአሥሩም ክፍለ ከተሞች የትራንስፖርት ስምሪት መዋቅር ተጠቅሞ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ በድሉ ሌሊሳ ለኢቲቪ ገልጸዋል።

ምክትል ሥራ አስኪያጁ ትርፍ በመጫን ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የሚሽቀዳደሙ ታክሲዎች ላይ እስከ አንድ ሺህ ብር ቅጣት እየተጣለባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህ መመሪያ ተግባራዊ እንዲደረግ ለስምሪት እና ቁጥጥር ባለሙያዎች የተላለፈ መሆኑንና አሠራሩን ጥሰው በተገኙት ላይ እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።

እስካሁን ባለው ሂደትም መመሪያውን ተግባራዊ በማያደርጉ ታክሲዎች ላይ የቅጣት እርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡

ችግሩ የትራንስፖርት ስምሪት ቁጥጥር በሚያደርጉ ባለሙያዎች ብቻ መቆጣጠር ባለመቻሉ የትራፊክ ማኔጅመንት መኪናዎችን ተጠቅመው በትብብር በአሥሩም ክፍለ ከተሞች ቅኝት እየተደረገ መሆኑን ሓላፊው ተናግረዋል፡፡

የታክሲ ተርሚናሎች ላይ የስምሪት ቁጥጥር ሠራተኞች፤ የታክሲ ተራ አስከባሪዎች እንዲሁም የትራፊክ ባለሞያዎች ትርፍ በሚጭኑ ባለታክሲዎች ላይ በጋራ ቁጥጥር እያደረጉ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ኅብረተሰቡ ትርፍ በመጫን ችግር የሚፈጥሩ ባለታክሲዎችን ለመጠቆም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የስክል ቁጥሮችን መጠቀም እንደሚቻል ባለሥልጣኑ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት:-

አራዳ ክ/ከተማ ………………… 0118333061

አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ……………..0118333210

ጉለሌ ክ/ከተማ ………………….0118333044

ልደታ ክ/ከተማ ………………… 0118333062

ኮልፌ ክ/ከተማ ………………….0118333039

ንፋስ ስልክ ክ/ከተማ …………… 0118333063

አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ……… 0118333067

ቂርቆስ ክ/ከተማ ………………. 0118333097

የካ ክ/ከተማ …………………… 0118333043 ቦሌ ክ/ከተማ ……………………0118333040

Leave a Reply