የከተማዋን የትራንስፖርት እንቅስቃሴና ስርዓት ለማሻሻል ለተቋሙ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ፡፡

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 30/2015 ዓ.ም ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ከብሉም በርግ ኢኒሼቲቭ ፎር ግሎባል ሮድ ሴፍ #Bloomberg ፣ ከወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት #WRIእና ከቫይታል ስትራቴጂ #VitalStrategies ጋር በመተባበር ለቢሮውና ለተጠሪ ተቋማቱ በአጠቃላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴና ስርዓት እንዲሁም በአገልገሎት አሰጣጥ ዙሪያ የአመራርነት /leader ship/ ስልጠና ሰጠ፡፡

የወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት #WRI የትራንስፖርት እቅድ ባለሙያ የሆኑት ኢንጅነር ጅሬኛ ሂርጳ የከተማዋን የትራንስፖርት እንቅስቃሴና ስርዓትን ለመምራት መሰራት ስለሚገቡ ተግባራት፣ የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂን በተመለከተና ዘርፉን ለማሳደግ የረጅም ጊዜ የስትራቴጂክ እቅዶች ላይ ትኩረት በማድረግና ተከታታይነት ያላቸው የግንዛቤ ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

ኢንጂነሩ አክለውም የከተማዋ 80 በመቶ ህብረተሰብ ህዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚ መሆኑን በመገንዘብ የትራንስፖርት አቅርቦትና ፍላጎትን ለማጣጣም በተለይ ደግሞ የብዙሃን ትራንስፖርትን በቴክኖሎጂ በመደገፍና ተደራሽ በማድረግ እንዲሁም የዲቢኤል ስራዎችን በትኩረት በመስራትና በማስፋፋት ለህብረተሰቡ በቂና ምቹ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት መሰራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት አርባን አናሊይስት የሆኑት ኢንጂነር ሰመረ ጅላሎ የከተማዋ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሰላማዊ ለማድረግ እንደ ችግር የሚታዩ ሰባት ርዕሰ ጉዳዮችን ለሰልጣኙ ያቀረቡ ሲሆን የመረጃ አያያዝና ማኔጅመንት፣ የፍሰት ማሳለጥ፣ የመንገድ ደህንነት ፣ የህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም፣ ከባለሶስትና አራት እግር /ባጃጅ/ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ፣ የቢአርቲ /BRT/ ወደ ተግባር በፍጥነት አለመግባት፣ ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ጋር ተያይዞ መተግባር ስለሚገባቸው ጉዳዮች በማንሳት ሰልጣኙ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዝ አድርገዋል፡፡

የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ስራዎች ላይ ዘርፉ የሚመለከታቸው ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት በመስራት በትራፊክ አደጋ የሚደርስ የሰውና የንብረት ጉዳትን መታደግ እንደሚገባና ትኩረት ተሰጥቷ መሰራት እንዳለበት ኢንጂነር ሰመረ ገልፀዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የከተማዋን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የተሻለ ለማድረግ ስልጠናው በቂ አቅም መፍጠር እንደሚችል ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply