=> ከተማዋ የምታመነጨው የገቢ ሁኔታ እና የሚሰበሰበው ገቢ ተመጣጣኝ አይደለም፤
=> ከለውጡ ወዲህ የገቢ መጠኑ በ3 እጥፍ አድጓል፤ በዚህም በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 30 ቢሊዮን ብር 100 ቢሊዮን ብር መድረስ ችሏል፤
=> የግብር መረብ ውስጥ ያልገቡ እና ግብር የሚሰውሩ በርካታ የንግድ አንቀሳቃሾች በከተማዋ ይገኛሉ፤
=> የቤት ግብር የዓለም ከተሞች የሚሰበስቡት የግብር ዓይነት ነው፤
=> አሁን እየተሰበሰበ የሚገኘው የቤት ኪራይና የቤት ግብር ደንብ ከ45 ዓመት በፊት የነበረ ደንብ ነው
=> የክፍያ መጠኑ አሁን ላይ ያለውን የኢኮኖሚ ሁኔታ እና እንቅስቃሴን መሰረት ያደረገ ነው፤
=> የግብር መጠኑ ጥናት ተደርጎ የግብር ስሌት ምጣኔው ቀድሞ የነበረው ሳይነካ ፤ የገንዘብ መጠኑ ነው ማሻሻያ የተደረገበት፤
=> መኖሪያ ቤቶች የሚከፍሉት በስሌቱ ተሰርቶ የሚመጣውን 50 በመቶ ብቻ ሲሆን የንግድ ቤቶችና መስርያ ቤቶች ደግሞ 75 በመቶ ብቻ ነው፤
=> በአዲስ አበባ ያለቁና አገልግሎት እየሰጡ ካሉ 800 ሺህ የመኖርያ ቤቶችና የንግድ ቤቶች ውስጥ 182 ሺህ ቤቶች ብቻ ነበሩ በግብር ስርዓት ውስጥ የነበሩት፤
=> የቤት ግብር የሚሰበሰበው የማይከፍለው ከሚከፍለው የሚበልጥ በመሆኑ እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ህብረተሰብ ክፍሎች ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ለማድረግ ነው፤
=> ለህዝቡ በድጎማ የሚቀርቡ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ፍትሃዊ የግብር ስርዓት ያስፈልጋል፤
=> የኑሮ ውድነት ጫና ያለበት ዝቅተኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ቢሆንም ግብር እየከፈለ ያለው ይሄው የማህበረሰብ ክፍል ነው፤
=> ከሚያዝያ ወር ጀምሮ 91 ሺህ ነዋሪዎች የከፈሉ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 62 በመቶ የሚሆነው የጋራ መኖርያ ቤት ነው፤
=> እስካሁን ከዚህ የግብር ዓይነት 600 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል፤
=> አብዛኞቹ የመኖሪያ ቤቶች ግብራቸውን ከፍለዋል፤
=> የአገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍ ተጨማሪ ሰራተኞች ተመድበው እየሰሩ ነው፤
=> በቀጣይ በቤት ግብር ውስጥ የማይካተቱ ዜጎችን በተመለከተ ጥናት እየተካሄደ ነው፤
=> የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር በየዓመቱ ከ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ለከተማዋ ነዋሪዎች ድጎማ ያደርጋል፤
=> በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉ የህዝቡን ኑሮ ማቅለያ ምርት የሚይዙ 5 ትልልቅ የገበያ ማዕከላት ውስጥ 2ቱ የተጠናቀቁ ሲሆን ሁለቱ በቅርቡ ይጠናቀቃሉ፤
=> የቤት ግብር ተከራይ ላይ ኪራይ ለመጨመር ምክንያት የሚሆን ጉዳይ አይደለም፤
=> የቤት ኪራይ የሚጨምሩ አከራዮችን ለመቆጣጠር ለክፍለከተሞች እና ወረዳዎች መመርያ ተላልፏል፤
=> ኢ-ፍትሃዊነትን ለማስተካከል ማህበረሰቡ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ ሊሰራ ይገባዋል፤
=> ለነዋሪዎች የመኖርያ ቤት አማራጮችን ለማቅረብ ከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፤