የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ በህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ አደረገ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2015 ዓ.ም በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ ግምት ውስጥ በማስገባት የትራንስፖርት ቢሮ በህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው ሃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ በጋዜጣዊ መግለጫው እንደተናገሩት አዲሱ የህዝብ ትራንስፖርት የታሪፍ ማሻሻያ ከጥር 13/2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

የታሪፍ ጭማሬ የተደረገውም በከተማዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ የሚኒባስ፣ የሚድ ባስ ማለትም ሀይገርና ቅጥቅጥ፣ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት እና የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ድርጅት መሆናቸው በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

ዘገባው፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው

Leave a Reply