የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ዛሬ ከታክሲና ሀይገር ባለንብረት ማህበራት ጋር የጋራ ውይይት አደረገ፡፡

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 2/2015 ዓ.ም፤ በውይይቱም በአገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮች በዋናነትም ከታሪፍ በላይ ማስከፈል፣ አቆራርጦ መጫን፣ ህግና ስርዓትን ጠብቆ ከመስራት አንጻር፣ ሙያዊ ስነምግባርና በታለመለት የነዳጅ ድጎማ ስርዓት ጋር ተያይዞ በሚታዩ የአሰራር ክፍተቶች ዙሪያ የጋራ ውይይት አድርገዋል፡፡

በመጨረሻም ማህበራቱ ባነሱዋቸው የድጋፍ እና የመልካም አስተደደር ጥያቄዋች ላይ ውይይት ተደርጎ የመፍትሄ አቅጣጫዎች የተቀመጠ ሲሆን፤ በውይይቱም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ፣ የትራንስፖርት ቢሮ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጆች፣ የታክሲና ሀይገር ባለንብረት ማህበራት አመራሮችና ተወካችና የትራንስፖርት አገልግሎት ክትትልና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ተሳታፊ ሆነዋል፡

Leave a Reply