የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የጠቅላላ ካውንስል አባላት የ2015 የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አደረገ።

አዲስ አበባ፤ ጥር 04/2015 ዓ/ም፤ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮው በስድስት ወራት በእቅድ ተይዘው የተከናወኑ ተግባራትንና የእቅድ አፈፃፀሙን በተቋሙ የመሰብሰብያ አዳራሽ ከጠቅላላ የፕሮሰስ ካውንስሉ አባላት ጋር በጋራ ተወያይቷል፡፡

ቢሮው በበጀት አመቱ በስድስት ወራት በእቅድ ተይዘው የተከናወኑ ተግባራትንና እቅድ አፈጻጸማቸውን ያየ ሲሆን፤ በሪፖርቱም በየቀኑ 10,315 ተሽከርካሪዎችን በቀን ለማሰማራት እቅድ የተያዘ ሲሆን በግማሽ ዓመቱ በአማካይ በየቀኑ 9,667 ተሸከርካሪዎች ማሰማራት መቻሉን፣ ባለው የአቅርቦት መጠን በቀን 3.1 ሚሊየን የጉዞ ፍላጎት መፍጠር ህዝብ ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ መቻሉንና በዚህም የእቅዱን 98 በመቶ መሳካት መቻሉ በሪፖርቱ የተመላከተ ሲሆን፤ ለዚህም ጠንካራ የኦፕሬሽንና የክትትል ስራ መሰራቱ ለእቅዱ የተሻለ መሆን በዋናነት ተገልፆል፡፡

በተመሳሳይ በሁሉም የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች የተፈፀመ ጥፋት ብዛት 33,298 ሲሆን ከዚህም 24,535,361ብር መሰብሰብ መቻሉን፤ እንዲሁም በዘርፉ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የተሰሩ ስራዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የተገልጋዩን እርካታ ማሳደግና ብልሹ አሰራርን በመታገል የተጠያቂነት ስርዓት መዘርጋት መቻሉ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ በግማሽ በጀት አመቱ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን በተለይ ተቋማዊ አደረጃጀትን ከመፍጠር፣ አገልግሎት አሰጣጡ ፍትሀዊና ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ መመሪያዎች መዘጋጀታቸው፣ ለተቋሙና ለተጠሪ ተቋማት ላሉ ባለሙያች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች መሰጠታቸው የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ የተሻለ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ከማድረግ አንፃር ሊበረታቱ እንጀሚገባ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በቀጣይ ቀሪ ስድስት ወራት በእቅድ ተይዘው ያልተከናወኑ ተግባራትን በማከል አሁን እየተመዘገቡ ያሉ ለውጦችን ማስቀጠል እንደሚገባ በመግለፅ፤ ዘርፉን በጋራ ለማሳደግና ለማዘመን በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ውጤታማ ተግባራትና ቅንጅታዊ አሰራሮችን በመዘርጋት የተሻለ ትራንስፖርት አገልግሎት በከተማዋ ለመስጠት በትኩረት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መስራት እንደሚገባ በአንክሮ ገልፀዋል፡

Leave a Reply