በብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡

በብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት፤ 8፣ 2012፤ በብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡

በከተማዋ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የተለያዩ የቅድመ መከላከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል።

በተለይ በአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ድርጅትና በሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ድርጅት የተሳፋሪዎችን ንጽህና ለመጠበቅ የእጅ ኬሚካል የማቅረብ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ተሳፋሪዎችም ወደ አውቶቡሶች ሲገቡ ድርጅቱ የሚያቀርበውን የእጅ ኬሚካል እጃቸው ላይ አድርገው እንዲገቡ ግንዛቤ እየተሰጠም ነው፡፡

አሽከርካሪዎቹም የእጅ ጓንት የሚጠቀሙ ሲሆን፥ የአውቶቡሶችን የውስጥ አካል በአልኮል በማጠብ የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ ጥረት ይደረጋል፡፡

ከዚህም ባለፈ ተሳፋሪዎች መስኮቶችን በመክፈትና አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የቫይረሱ ስርጭት መግታት ይገባል፡፡

የትራንስፖርት ቢሮም የቫይረስን ስርጭት መጠን ለመቀነስ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል፡፡

Leave a Reply