የትራፊክ ቁጥጥርና የፓርኪንግ አስተዳደር ሥርዓትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እየተሰራ ነው።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከኢንፍራ ቴክ የግል ኩባንያ ጋር በጋራ እያለማ ባለው የፓርኪንግ እና የትራፊክ ቅጣት ሲስተም 97 በመቶ መጠናቀቁ ተገለፀ።

እየለማ ባለው ቴክኖሎጂም የከተማ አስተዳደሩ የአሽከርካሪዎችን ሙሉ መረጃ መሰብሰቡንና በቀጣይ ቀሪ ስራዎች እንዲሞሉና ወደ ስራ እንዲገባ በውይይቱ ተጠቁሟል።

በውይይቱም ከአዲስ አበባ ትራንስርት ቢሮ፣ ኢንፍራ ቴክ የግል ኩባንያ እና ከአሽከርካሪ ተሸከርካሪ ቁጥጥር ባለስልጣን የተውጣጡ ባለሙያዎችና የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ምንጭ:-ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

Leave a Reply