የትራፊክ መጨናነቅን ለማሻሻል እና የመንገድ የተሻለ አጠቃቀምን ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ውይይት ተካሄደ።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ በተገኙበት የትራፊክ መጨናነቅን ለማሻሻል እና የመንገድ የተሻለ አጠቃቀምን ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ጥናት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

የትናቱ ዓላማ በአዲስ አበባ ከተማ በተለይ የመውጭያ እና መግቢያ ሰዓት (pick hour) ላይ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቅረፍ እና ዘላቂ መፍትሔ በማበጀት ምቹና የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንድኖር ለማድረግ ስለመሆኑ ተመላክቷል፡፡

ጥናቱን የተካሄደው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የጥናት ቡድኖች ጋር ሲሆን በመንገድ አጠቃቀም ዙሪያ የሚስተዋሉ ያልተገቡ ልምምዶችን እና የትራፊክ መጨናነቅን ሊቀርፍ የሚል ጥናት መሆኑ ተነግሯል፡፡

በመድረኩ እንደተገለፀው በጥናት ላይ የተመሠረቱና የሌሎች ሀገራት ተሞክሮዎችን ያገናዘቡ ስልታዊ አሠራሮችን በመተግበር በአዲስ አበባ የሚታየውን የትራንስፖርት ዘርፍ ችግሮች ለመፍታት ጥናቱ ስለመካሄዱ የተጠቆመ ሲሆን ይህም ጥናት አስፈላጊ ግብአት ታክሎበት በአጭር ጊዜ ወደ ተግባር የሚቀየር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ የጥናቱን ውጤት በሚመለከት እደገለፁት የቀረበው የጥናቱ ውጤት ጥሩ መሆኑን እና የአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ መጨናነቅን ለማሻሻል በአጭር ጊዜ መሰራት ያለበት የወጡት ነባሩን ህጎች በቁርጠኝነት ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተለይ በጭር ጊዜ መሰራት ያለባቸው የትራፊክ ፍሰቱ እንዳይሳለጥ የሚያደርጉ እንደ ጎሚስታ፣ የመንገድ ዳር ንግድ እና አሰፋልት ዳር የሚቆሙ ተሸከርካሪዎችን ስርዓት ማስያዝ እንደሚገባ ክቡር ሚኒስትሩ ጨምሮ ገልፀዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ፣ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሐሰን፣ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኬያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ኬይረዲን ፣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ፣ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ክበበው ሚደክሳ እና የሚኒስቴር መስሪያቤቱ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

@የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር

Leave a Reply