የትራንስፖርት ቢሮ ለ110 አዳዲስ የአንበሳ ከተማ አውቶብስ የስምሪት መስመሮችን ሰጠ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 09፤ 2015 አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት በ127 የስምሪት መስመሮች አገልግሎት በመስጠት የከተማችንን የህዝብ ትራንስፖርት ፍላጎት ለማርካት እየሰራ መሆኑ ያታወቃል፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ፍትሀዊና ተደራሽ ለማድረግ እንዲያስችል በጥናት የለያቸውን አስራ ስድስት (16) የአውቶብስ የስምሪት መስመሮችን በመለየት ለአንድ መቶ አስር (110) አዳዲስ አውቶብሶች ስምሪት ሰጥቷል፡፡

የአውቶብሶች የስምሪት መስመሮቹ በጥናት ሲለዩ በዋናነት መሠረት ያደረገው የህዝብ ትራንስፖርት ፍላጎት ያለባቸውን ቦታዎች ታሳቢ በማድረግ፣ አዳዲስ የመኖሪያ ቦታዎችና ኮንዶሚኒየም ቤቶችን መሰረት ያደረገ፣ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የአዳዲስ መስመሮች ይከፈትልንን ጥያቄ መነሻ በማድረግ፣ የረጃጅም መስመሮች ባለመኖራቸው ህብረተሰቡ በመሀል የከተማዋ ስፍራዎች የሚፈጥረውን ረጃጅም ሰልፎች ለማስቀረትና በአነስተኛ ወጪ ምቾቱን ጠብቆ በአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ነው፡፡

በከተማዋ አገልግሎት እየተሰጠባቸው ያሉት መስመሮች አዳዲስና ቀደም ሲል አገልግሎት ሲሰጥባቸው የነበሩ ሲሆኑ፤ ከዩኒሳ በመገናኛ 6 ኪሎ፣ ከአስኮ /በሳንሱሲ/ ፒያሳ መገናኛ፣ ከአየር ጤና በጦር ሃይሎች መገናኛ፣ ከአዲሱ ገበያ በእስቴድየም ጉተራ ሳሪስ፣ ከቱሉ ዲምቱ በሜክሲኮ ፒያሳ፣ ከኮየፈጬ በጋርመንት ሜክሲኮ፣ ከቃሊቲ በለገሃር መርካቶ፣ ከየካ አባዶ በመገናኛ ሜክሲኮ፣ ከየካ አባዶ በመገናኛ ፒያሳ፣ ከቦሌ አራብሳ በካራ ወሰን መገናኛ ሜክሲኮ፣ ከቦሌ አራብሳ በካራ ወሰን ፒያሳ፣ ከኮየ ፈጬ በመገናኛ ፒያሳ፣ ከጎሮ በመገናኛ ገርጂ ሜክሲኮ፣ ከጀሞ 2 በጀርመን ጎፋ ቂርቆስ ለገሃር መገናኛ፣ ከሰሚት ኮንዶሚኒየም በ ሲኤምሲ መገኛ 4 ኪሎ ፒያሳ እና ከኮየፈጬ በጎሮ መገናኛ መመደባቸውን ትራንስፖርት ቢሮው አስታውቋል፡፡

እነዚህን አዳዲስ መስመሮች መከፈታቸው ህብረተሰቡ ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ ከመስጠቱን ባለፈ በተመጣጣን ዋጋ ዘመናዊና ምቹ በሆኑ አውቶብሶች አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ቢሮው እየገለፀ፤ ህብረተሰቡም የብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎትን የመጠቀም ባህሉን በእጅጉ ሊያሻሽል እንደሚገባና ለአጫጭር የጉዞ ርቀቶች የእግር መንገድን እንዲያዘወትር መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

ዘገባው፡-በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!

Leave a Reply