የብስክሌት መጋለቢያ መስመር ላይ ምልክትና ማመላከቻዎች እየተተከሉ ይገኛሉ

(ጥቅምት 05/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ)፡- በአዲስ አበባ ከተማ ከማዘጋጃ ቤት መስቀል አደባባይ በዘመናዊ መልክ ተገንብቶ ለተሽከርካሪዎች፣ ለእግረኞች እና ለብስክሌት ጋላቢዎች ክፍት የሆነው መንገድ ላይ አስፈላጊ ምልክቶች በመተከል ላይ ናቸው፡፡

ምልክቶቹ ብስክሌት ጋላቢዎች በሚጠቀሙባቸው መንገዶች መጋጠሚያዎች ላይ ተሽከርካሪዎች መንገዱን ሲያቋርጡ እና መስቀለኛ መንገዶች አከባቢ ሲተላለፉ በጥንቃቄ እና በዝግታ እንዲጓዙ የሚያደርጉ ናቸው።

ከመስቀል አደባባይ ለገሃር፣ በቸርችል ጎዳና እስከ ማዘጋጃ ቤት ባለው መንገድ የተተከሉ ምልክቶች ብስክሌት ተጠቃሚዎች የሚጠቁሙ እና በዝግታ እንዲያሽከረክሩ ወይም አሽከርካሪዎች ቆም ብለው ቅድሚያ እንዲሰጡ የሚያደርጉ በአጠቃላይ 26 ምልክቶች ናቸው።

ኤጀንሲው በከተማዋ የብስክሌት ተጠቃሚዎችን ለማበረተታት እና ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ መሰል ተግባራትን ቀደም ብለው በተሰሩ መንገዶችም ሆነ ለብስክሌት ጋላቢዎች የሚዘጋጁ መንገዶች ላይ ተመሳሳይ ስራዎችን በመስራት ብስክሌተኞን ከትራፊክ አደጋ እንዲጠበቁ ለማድረግ እንደሚሰራ በኤጀንሲው የመንገድ ትራፊክ ኢንጂነሪንግና ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ መርጋ ሰፈራ ገልፀዋል የከተማዋ ነዋሪዎች ብስክሌት መጠሸምን ልምድ እንዲያደርግ ኤጀንሲው ያበረታታል ብለዋል።

አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስና ውብ እናደርጋታለን!

Leave a Reply