የለውጡ ፍሬያማ ጉዞ ለተጀመረበት 6ኛ ዓመት እና የኢትዮጵያዊነት መሰረት ለሆነው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 13ኛ ዓመት እንኳን አደረሣችሁ! አደረሰን!

በለውጡ መሃንድስ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የለውጥ ኃይል በብዙ ውስጣዊ እና ውጫዊ ፈተና ውስጥ ሆኖ በርካታ ስኬቶችን በመጎናጸፍ ላይ ይገኛል። ከነዚህም ፦

የህዳሴ ግድባችን ማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ መድረስ ፣ ኢትዮጵያ አረንጏዴ ለብሳ ከስንዴ አስመጭነት ወደ ላኪነት የተሸጋገረችበት ፣ከ 128 አመታት በኋላ የአድዋ ድል መታሰቢያ ግንባታ ተጠናቆ የተመረቀበት፣ከተማችን አዲስ አበባ ትኩረት አግኝታ በርካታ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል መሆን ጀመረችበት እና በሰው ተኮር ስራዎቻችንም ማኅበራዊ ፍትህ ያነገስንበት ነው የለዉጡ አመታት።

ቃል በተግባር ተመንዝሮ ኢትዮጵያችን በሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት የደመቀች ዕድገትዋ መፋጠን የጀመረችበት ፣ በመፍጠንና መፍጠር ዕዳዋ እየቀነሰ ምንዳዋ እየጨመረ የመጣች ሀገር እየሆነች ነው።

ለፈተናዎቻችን ሳንንበረከክ ከችግሮቻችን ባሻገር የበለጸገችዋ ኢትዮጵያን ለመገንባት ተደምረን የጀመርነውን ጉዞ ዳር ለማድረስ በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን!

ምድራዊ ሃይል ሊያስቆመው የማይችለውን የብልጽግና ጉዞ ገብቷችሁ ድጋፋችሁንና ደስታችሁን ለገለፃችሁ ምስጋናዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

Leave a Reply