ከትምህርት ቤት መከፋት ጋር በተያያዘ የትራፊክ ፍሰት መጨናናቅ እንዳይፈጠር እየተሰራ ነው

የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አንበሳ የከተማ አውቶቡስ ድርጅት እና ሸገር ባስ በከተማችን ቀልጣፋ እና ፈጣን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች ከትራፊክ ፖሊሶች ጋር በመሆን የአውቶቡሶቹ ምልልስ ፈጣን፣ ቀላል እና ቀልጣፋ እንዲሆን በሰዓት የተገደበ ለብዙሃን ትራንስፖርት የተፈቀዱ መንገዶችን ህግ በማስከበር ላይ ይገኛሉ።

የኤጀንሲው የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎቹ ትምህርት ቤቶች አካባቢም ጥብቅ የትራፊክ ህግ እና ስርዓትን የማስከበር ስራ በማከናወን ላይ የሚገኙ ሲሆን ፍሰቱን የማስተናበሩንም ስራ በመከወን ላይ ናቸው።

በትምህርት መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ላይ የሚስተዋለውን የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅን ለመቅረፍ ሁሉንም ሰው የሚመለከት በመሆኑ ኤጀንሲው በተለይ ባለድርሻ አካላትን በመፍትሄው ላይ ሲያወያይ ቆይቷል።

የትምህርት ቤት ማህበረሰብ በተለይ ዕሳና መምህራኖች፣ የትምህርት ቤቶቹ ባለቤቶች እና የተማሪ ወላጆች ጉልህ ሚና ስላላቸው የኤጀንሲው አምስቱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የትራፊክ ፍሰት መጨናናቅ ከሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ከተለዩ 42 ት/ቤቶች ጋር በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

ኤጀንሲው ችግሩን ለመቅረፍ ባለድርሻ አካላት ባሳተፈ መልኩ የመፍትሄ ሀሳብ ላይ ከመወያየት ባሻገር ባለድርሻ ተቋማትን ባሳተፈ መልክ የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎችንም አከናውኗል።

በተለይ በተለዩት 42 ት/ቤቶች አካባቢ የምህንድስና ማሻሻያዎች የተተገበሩ ሲሆን አስፈላጊ የትራፊክ ምልክት እና ማመላከቻዎች ተከላንም አከናውኗል። በአካባቢዎቹ እና በየትምህርት ቤቶቹ የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራም በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

@TMA

Leave a Reply