ከመገናኛ አዲሱ ገበያ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ሲታይ ለነበረው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ ተሰጠ፡፡

(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ግንቦት 15/2016ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በየካ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ከመገናኛ – አዲሱ ገበያ የጉዞ መስመር ቀድሞ በሚኒባስ ታክሲ ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎቱ እንዲሰጥ መደረጉን ገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ዳዊት ዘለቀ ህብረተሰቡ ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር በተገናኘ በዋናነትም ከማቆራረጥና ከታሪፍ በላይ ማስከፈል ጋር ተያይዞ በመስመሩ የሚስተዋለውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጠው በጠየቀው መሰረትና ቢሮውም ችግሩን ከቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ጋር በጋራ መለየቱን ገልፀዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን አገልግሎቱ በብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ በሆኑት የአደይ አበባ አውቶብስ፣ የሚዲባስ በተለምዶ ቅጥቅጥ አውቶብሶችና የከተማ አውቶብሶችን በድምሩ 32 የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችን መድቦ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ችግሩን መፈታት ተችሏል ብለዋል፡፡

ህብረተሰቡም ቢሮው ባቀረባቸው አማራጭ የብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲጠቀሙ ያሳውቃል፡፡

Leave a Reply