ከለቡ-ጀሞ በተሰራው የብስክሌት ኮሪደር የተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡

ከለቡ-ጀሞ በተሰራው የብስክሌት ኮሪደር የተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26፤ 2012፤ከለቡ-ጀሞ በተሰራው የብስክሌት ኮሪደር የተጠቃሚዎች ቁጥር በ10 እጥፍ መጨመሩን የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአራት ዙር የተሰበሰበው መረጃ እንደሚያሳየው የብስክሌት ተጠቃሚዎች ቁጥር ጠዋት ከ 3 ወደ 30፣ ቀትር ከ2 ወደ 46 እና ማታ ከ4 ወደ 35 መጨመሩን መረጃው ያሳያል፡፡

በተመሳሳይ ኮሪደሩ ስራ ከጀመረት ጊዜ ጀመሮ ብስክሌትን በግል ንብረትነት የገዙ ሰዎች ቁጥርም በሶስት እጥፍ ጨምሯል፡፡

በሌላ በኩል በኮሪደሩ የሙከራ ትግበራ ምክንያት በትራፊክ ይዘቱና በተሽከርካሪዎች ፍጥነት ላይ ምንም አይነት ተጽዕኖ እንዳልፈጠረ መረጃው ያመለክታል፡፡

በተጨማሪም ከለቡ ወደ ጀሞ አቅጣጫ የሚያልፉ የተሽከርካሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ተመላክቷል፡፡

በመሆኑም ቀትር ከ1249 ወደ 2514 እና ማታ ከ1371 ወደ 1409 ሊጨምር ችሏል፡፡

ኮሪደሩ ከመሰራቱ በፊት የብስክሌት ተጠቃሚዎች ስለደህንነታቸው የነበረው ስጋት በእጥፍ መቀነሱ ተነስቷል፡፡ 

ይህም የኮሮና ቫይረስን ከመከላከል ጋር ተያይዞ የብስክሌት ትራንስፖርት እንደአማራጭ የትራንስፖርት ዘዴ የመጠቀም ፍላጎት መጨመሩም በመረጃ ተጠቅሷል፡፡

ኮሪደሩ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ጋር በመቀናጀት ሕግ የማስከበር ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

2.7 ኪሜ ርዝመት የሚሸፍነው ከለቡ-ጀሞ የተሰራው ባለ ሁለት አቅጣጫ የብስክሌት ኮሪደር ከሚያዝያ 8 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለስድስት ወራት በሙከራ ላይ ይገኛል፡፡

Leave a Reply